Skip to main content
ወደ MC እንኳን በደህና መጡ!

ወደ MC እንኳን በደህና መጡ!

ዲግሪ ወይም አዲስ የባለሙያ ክህሎት መማር ከፈለጉ፣ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የመጀመሪያውን እርምጃ እንዲወስዱ ሊረዳዎ ይችላል። እንደ ኤምሲ (Montgomery College) ተማሪ፣ አላማዎችዎ ጋር እንዲደርሱ የሚያስፈልግዎትን ድጋፍ፣ መመሪያ፣ እና እድሎችን ያገኛሉ።

 

Montgomery College is the most diverse community college in the continental US. We participated in the #YouAreWelcomeHere campaign to affirm that we welcome students from all backgrounds.

በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ገብቼ መማር እፈልጋለሁ። የት ልጀምር?

በአላማዎ ላይ ተመስርቶ፣ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ (MC) ብዙ አማራጮች አሉት። ነጻ የሆኑ መሰረታዊ  የእንግሊዝኛ ትምህርት (ESL) እና ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲፕሎማ ጋር የሚመጣጠን ደረጃ የሚያገኙበት የጂኢዲ (GED) ኮርሶች አሉ። እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሆኑ የእንግሊዝኛ ትምህርት ቤቶችም አሉ። በስራ ሃይል ማጎልበቻ እና ቀጣይ ትምህርት (WDCE) ፕሮግራም የሚሰጡ አጫጭር የስልጠና ፕሮግራሞች እና ሰርቲፊኬቶችን፣ እንዲሁም ወደ ኮሌጅ ዲግሪ የሚያመሩ የሙሉ ሰዓት የሁለት አመት ጥናቶችም ይሰጣሉ። በነዚህ እና በሌሎች ብዙ የትምህርት መስኮች እንዴት መከታተል እንደሚችሉ ለማወቅ፣ በ 240-567-5000 ይደውሉ (አስተርጓሚዎች ይገኛሉ)።

የተማሪ ቪዛ ወይም የ I-20 ቅጽን ከፈልጉ፣ እዚህ ይጫኑ።

ምን አይነት ኮርሶች ነው የሚሰጡት?

ሞንትጎመሪ ኮሌጅ   ክሬዲት ያላቸውን እና የሌላቸውን ኮርሶች ያቀርባል።

 ልዩነቱ ምንድን ነው?

ክሬዲት ያላቸው ኮርሶች ሰርቲፊኬት ውይም የኮሌጅ ዲግሪ ለማግኘት የኮሌጅ ክሬዲቶች ለመቀብል ለሚፈልጉ ተማሪዎች የሚሆኑ ናቸው፤ ወይም ወደሌላ ዩኒቨርሲቲ መተላለፍ የሚችሉ ኮርሶችን ለሚወስዱ ተማሪዎች የሚሆን ነው። በክሬዲት ኮርስ ማውጫ ውስጥ ክፍሎችን እና ፕሮግራሞችን ይፈልጉ

ክሬዲት የሌላቸው ኮርሶች የሚሆኑት ጠቅላላ እውቀት ለማግኘት ወይም በተወሰኑ አካባቢዎች ያላቸውን እውቀት ለማስፋት፣ ሙያ ለመማር፣ ወይም የግል ፍላጎትን ለመከተል ለሚፈልጉ ተማሪዎች ነው። ክሬዲት የሌላቸው ኮርሶች ወደ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ለመቀበል መዋል አይችሉም፤ ነገር ግን ተማሪዎች ክሬዲት የሌላቸውን ኮርሶች በመውሰድ የቀጣይ ትምህርት አካሎችን ወይም ሙያ ለማከናወን የሚረዱ ሰርቲፊኬቶችን ለማግኘት መውሰድ ይችላሉ። ክሬዲት በሌላቸው ኮርስ ማውጫ (WDCE) ውስጥ ኮርሶች እና ፕሮግራሞችን ይፈልጉ። 

እንግሊዘኛዬን እንዴት ማሻሻል እችላለሁ?

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎቶችዎን ለማሻሻል ስለክሬዲት እና ክሬዲት የሌላቸው ኮርሶች አማራጮች ተጨማሪ ያንብቡ።

የመጀመሪያ እርምጃዎች፥ እንዴት መመዝገብ ይቻላል

ከዚህ የሚከተሉት ወደ መጀመሪያው የኤምሲ ትምህርት የሚወስዱዎ ቀላል እርምጃዎች ናቸው።

እነዚህ እርምጃዎች የክሬዲት ክፍሎችን ለመውሰድ ለሚፈልጉ አዲስ ተማሪዎች ናቸው።  የክሬዲት ተማሪ ከሆኑ፣  ለትምህርት እንዴት መመዝገብ ይቻላል የሚለውን ይዩ።

የትምህርት ፕሮግራም ቅደም ተከተሎችን  እና  ፕሮግራሞችን በኦንላይን (Online) ማየት ይችላሉ።

ክሬዲት ለሌላቸው (WDCE) ክፍሎች፣ የሚከተሉትን እርምጃዎች መከተል የለብዎትም፥ የሚፈልጉትን ትምህርት መርጠው ከዛም  ተመዝግበው መክፈል ነው ያለብዎት።

ለክሬዲት ክፍሎች የምዝገባ ሂደት

እርምጃ አንድ፥ ማመልከት

የመግቢያ ማመልከቻውን ይሙሉ።

የሚጠየቅ

  • ለመግባት ያመልክቱ
  • ከትምሕርት ሚንስትር የሚሰጠዉን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትራንስክሪብትን ወደ መግቢያ ቢሮ ይላኩ።

ወደ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ  ለመግባት  ለማንኛውም ከታወቀ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተመረቀ፣ የአጠቃላይ የዲፕሎማ መስተካከያ (ጂኢዲ) ፈተናን በአጥጋቢ ሁኔታ ያጠናቀቀ፣ ወይም ቢያንስ 16 እድሜ የሆነ እና ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመረቀ ወይም ለለቀቀ ተማሪ ለመግባት ክፍት ነው። መደበኛ የፈተና ውጤቶች (ለምሳሌ SAT፣ ACT) ለመግባት የሚጠየቁ አይደሉም፤ ነገር ግን የክፍል ምደባን ለማወቅ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። 

አማራጭ የሆነ

በኮሌጁ ያሉ አንዳንድ ፕሮግራሞች ተጨማሪ የመግቢያ መጠይቆች እና ወይም የጊዜ ገድቦች አሉዋቸው። ለዝርዝሩ እያንዳንዱን ፕሮግራም ይመልከቱ፥ 

እርምጃ ሁለት፥ አካውንትዎን በመክፈት ምደባዎን ይወቁ

የ MyMC አካውንትዎን እና MyMC ኢሜይሎን ይፍጠሩ። ከዛም የምደባ ፈተና መውሰድ እንደሚገባዎ ያረጋግጡ።

እርምጃ ሁለት፥ አካውንትዎን በመክፈት ምደባዎን ይወቁ

የሚጠየቅ

  • የ MyMC አካውንቶን ይቀበሉ፥ ወደ MyMC በመሄድ  "አካውንቶን ይቀበሉ" የሚለው ላይ ይጫኑ። የ MC ተማሪ መታወቂያዎን እና የ M ቁጥር (Mን ጨምሮ ዘጠኝ ፊደሎች) እንዲያስገቡ ይጠየቃሉ።
  • ወደ MyMC ከገቡ በሁዋላ፣ የኢሜይል ምልክቱን በመጫን የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ኢሜይል አካውንቶን ይፍጠሩ። ይህ MC ከርስዎ ጋር የሚገናኝበት መንገድ ነው።
  • ምደባ ፈተናዎችን መውሰድ እንደሚገባዎ ያረጋግጡ። የ Accuplacer  ወይም የ Accuplacer ESL  ፈተና ሊወስዱ፣ ወይም ከመውሰድ ነጻ ሊሆኑ ይችላሉ። ብዙ ከውጭ የመጡ ሰዎች ESL Accuplacer ፈተና  መውሰድ ሊኖርባቸው ይችላል
እርምጃሶስት፥መተዋወቂያዎንአሙዋልተውከአማካሪዎጋርቀጠሮይያዙ

የትምሕርት ቤት መታወቂያ ያውጡ። ከትምሕርት አማካሪዎ ጋር ይገናኙ።

Complete orientation and meet counselor

የሚጠየቅ

እርምጃአራት፥ለክፍሎችተመዝግበውይክፈሉ

ለክፍሎችዎተመዝግበውክፍያዎንበጊዜመፈጸምዎንያረጋግጡ።

Register and pay for classes

የሚጠየቅ

አሁን፣ለሴሚስተሩእንዘጋጅ፥

 
ሞንትጎመሪ ኮሌጅ ለመማር ምን ያህል መክፈል አለብኝ?

በእውነቱ፣ ከሚያስቡት በታች ነው! እዚህ ትምህርት የሚከፈለው ከሌሎች ብዙ ዩኒቨርሲቲዎች ያነሰ ነው። በመማሪያ ወጭዎች ላይ ከባለ አራት አመት የህዝብ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ሲነጻጸር እስከ 50% ድረስ ያነሰ ወጪ አለው።

ክሬዲት ክፍሎች

ለክሬዲት ክፍሎች የመማሪያ እና ክፍያዎች የሚለያዩ ሲሆን፣ የሚወሰነውም በሚወስዱት የክሬዲት ሰዓቶች ቁጥር፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ፣ ወይም በሌላ የሜሪላንድ ካውንቲ፣ ወይም ከስቴት ውጪ ነዋሪነትዎ ነው። ለቴክኒካዊ ስራ ብቁ ለመሆን ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመቀበል በሚወስዱት የክሬዲት ሰዓቶች ቁጥር ላይ ተመስርቶ መማሪያ ክፍያ ይከፍላሉ። ለምሳሌ፣ የሙሉ ሰዓት ተማሪ ለ 12 ክሬዲቶች፣ እና በተጨማሪም ለመጽሃፎች ወጪ መክፈል ይኖርበታል። የአሁኑን የመማሪያ ወጪ ተመኖች ይመልከቱ

ክሬዲት የሌላቸው ክፍሎች

ክሬዲት የሌላቸው ክፍሎች የመማሪያ ወጪ የሚወሰነው በጥናቱ ፕሮግራም ወይም መውሰድ በሚፈልጉት ኮርሶች አይነት ነው። ስለ ክሬዲት የሌላቸው ትምህርቶች ወጪ ተጨማሪ መረጃ፣ ይህንን ገጽ ይጎብኙ እና የሚፈልጉትን ኮርስ ይምረጡ። ለወጪ መረጃ በተጨማሪም በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ፥ 240-567-5188.

ወጪዎቹን ለመክፈል የፌዴራል የገንዘብ እርዳታ (ፋፍሳ) አለ?

ክሬዲት ክፍሎች

ለጥቅማ ጥቅሞቹ ብቁ ከሆኑ ለገንዘብ እርዳታ ማመልከት ይችላሉ

ለተማሪዎች የተዘጋጁ የተለያዩ የገንዘብ እርዳታ ፕሮግራሞች አሉ። በዚህ ገጽ ስለ ገንዘብ እርዳታ አይነቶች የበለጠ መረጃ ያገኛሉ

ለነዚህ የእርዳታ ፕሮግራሞች ብቁ መሆንዎን ለማወቅ፣ በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ገንዘብ እርዳታ ቢሮ፣ በዩናይትድ ስቴተስ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ እና በኢንተርኔት ላይ የሚገኘውን የፌዴራል ተማሪ እርዳታ ነጻ ማመልከቻ (FAFSA) መሙላት አለብዎት። ይህ ማመልከቻ ነጻ መሆኑን ልብ ይበሉ፤ እናም ለማንም ሰው መሙላት እንዲረዳዎ መክፈል አይኖርብዎትም። ለዚህ ማመልከቻ ለመሙላት ድጋፍ ከፈለጉ፣ የገንዘብ እርዳታ ቢሮን በ 240-567-5100 ይደውሉ፣ ወይም በማንኛውም ካምፓሶች ባሉት ቢሮዎቻችን አንዱ ለግል ትኩረት ይጎብኙን።

ሞንትጎመሪ ኮሌጅ ነጻ የትምህርት እድሎች አሉት። ለሞንትጎመሪ ኮሌጅ ነጻ የትምህርት እድሎች ለማመልከት፣ በዚህ ገጽ ላይ ያሉትን የማመልከቻ ቅጾችን ይሙሉ

ነጻ የትምህርት እድሎች በተጨማሪም በግል ኩባኒያዎች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በኩል ይገኛሉ። ስለ ነጻ የትምህርት እድሎች መረጃ በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ገንዘብ እርዳታ ቢሮ ወይም ይህንን ገጽ በመጎብኘት ማግኘት ይቻላል

ክሬዲት የሌላቸው ትምህርቶች

ፌዴራል ገንዘብ እርዳታ (FAFSA) እነዚህን ኮርሶች ኣይሸፍንም። ነገር ግን፣ ሊያገኙዋቸው የሚችሉ አንዳንድ ነጻ የትምህርት እድሎች አሉ። ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ይጫኑ

የክፍያ እቅዶች አሉ?

ሞንትጎመሪ ኮሌጅ የሚያቀርበው የክፍያ እቅድ ተማሪዎች የመማሪያን ወጪ በሴሚስተሩ ወቅት ለሶስት ክፍያዎች ከፋፍለው እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው። አስቀድመው ከተመዘገቡ፣ ተጨማሪ መመቻቸቶች ይኖርዎታል። የገንዘብ ያዡን በመማሪያ ወጪ ክፍያ እቅዶች (ቲአይ ፒ) እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ይጠይቁ ወይም ይህንን ገጽ ለተጨማሪ መረጃ ይጎብኙ

የዲፕሎማዎች፣ የክሬዲት ማስተላለፍ እና ለቀደሙ እውቀት ክሬዲት ግምገማ

ከኮሌጅ ውጭ የተማሩትን በመጠቀም ዲግሪዎን ለማግኘት ጊዜ እና ገንዘብዎን ይቆጥቡ።

(Montgomery College) ጥናቶችዎን በኤምሲ ለማጠናቀቅ በሌሎች ኢንስቲትዩቶች ያገኙትን ክሬዲቶች ለመጠቀም እድሎችን ያቀርብልዎታል። ከሌሎች ኢንስቲትዩቶች የበፊቶቹን ክሬዲቶች ማስተላለፍ ይችላሉ፤ እንዲሁም ፈተናዎችን መውሰድ እና ወይም የውትድርና አገልግሎትን ጨምሮ ለስራ ልምዶች ክሬዲቶችን ማግኘት ይችላሉ።

 

በፕሮግራም ቢመዘገቡ ወይም እንደ አዲስ ተማሪ በፕሮግራም ለመመዝገብ ፈልገው ቢሆንም ሁሉም የኤምሲ (Montgomery College) ተማሪዎች ይህንን እድል መጠቀም ይችላሉ።

የማህበረሰብ ተሳትፎ ማእከሎች (Community Engagment Centers)

የበለጠ ምቹ ከሆነልዎት፣ ከማህበረሰብ ተሳትፎ ማእከሎች አንዱን (በጋይተርስበርግ ቤተ መጻህፍት (Gaithersburg Library እና በኢስት ካውንቲ East County Regional Center) የአካባቢ አገልግሎት ማእከል) ይጎብኙ። ለብዙ ጥያቄዎችዎ መልስ ማግኘት ይችላሉ፤ እንዲሁም በነዚህ ማእከሎች ክሬዲት የሌላቸውን ለሞያ የሚያበቃ ሰርተፊኬት ትምህርቶች መውሰድ ይችላሉ። Gaithersburg Library; 18330 Montgomery Village Ave Gaithersburg MD 20879. East county regional Center address 3300 Briggs Chaney RD Silver Spring Maryland 20904

የአማርኛ ቪዲዮዎች

How to find the Resource Guide for Short-Term Courses (Amharic)
MC's Short-term career courses (Amharic)
Resume Builder Tutorial (Amharic)
Interview Tips in Amharic